የድነት መልዕክቶች

ሀ.ሚስጥረ ድነት

    ”ወይቤ፡ መጽሐፍ፡ ኩሉ፡ ዘየአምን፡ ቦቱ፡ የሐዩ ” ሮሜ.10፡11

      በክርስትና ውስጥ ሊታወቁ የሚገባቸው ትክክለኛ የደህንነት /ድነት/ መሰረቶች እና ሊመለሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

 በቅድሚያ ድነት የምንለው የነፍስ ድነትን ነው፡፡ ይኸውም ሰው በሐጢያተኝነቱ ሊቀበለው ካለ ፍርድና ኩነኔ አምልጦ በክርስቶስ የዘላለም ህይወትን ስለ ሚወርስበት ጉዳይ ነው፡፡

1- ሁሉም ሰው ሐጢያትን ሰርቶአል?

“ልዩነት የለምና ሁሉ ኃጢያትን ሰርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤በኢየሱስ  ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ፡፡”  በግዕዙ እንዲህ ይላል / ወኢፈለጣ፡ ወኢሌ ለየ፡፡እስመ፡ ኩሉሙ፡ አበሱ፡ወጌጋዩ፡ ወኀደጉ፡ ስብሐተ :እግዚአብሔር /   ሮሜ 3፤23       

 “ልዩነት የለም” የሚለው ቃል የሰውን ስጋ ለብሶ ከመጣው ከጌታችን በስተቀር ስጋን የለበሰን ሁሉ ሰው ማለት ነው፡፡ የሐጢያት መንስኤውም አንድም የአዳም አለመታዘዝ ሲሆን / ሮሜ .5፤19/ :ቀጥሎም ሰው ሁሉ በነፍስ ወከፍ ያደረገው ሐጢያት ነው፡፡

2- የሐጢያት ደሞዝ  ምንድን ነው?

“የኀጢያት ደሞዝ ሞት ነውና ::የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ህይወት ነው፡፡” ሮሜ.6፤20 : ሐጢይት ልክ  እንደማንኛውም ስራ የራሱ ደሞዝ አለው፡፡ ክፍያው ከበድ ያለ ስለሆነም ነው ንስሀ መግባት አስፈላጊ የሆነው፡፡ የኃጢያት ደሞዝ የዘላለም ሞት ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ የዘላለም ሞት ሊታደገን  ፡እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለእኛ ሰጠን /ዮሐ.3፤16/፡፡

3- ከሞት ፍርድ እንዴት ማምለጥ ይቻላል?

የዮሐንስ ወንጌል ም.3 ቁ 16-18 ሲናገር ” በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ  ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ፤ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አላከውምና፡ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ  በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል፡፡ ” ከላይ እንደተጠቀሰው  ከዘላለም ፍርድ ና ከዘላለም ሞት ለመዳን መንገዱ በክርስቶስ ማመን ነው፡፡ 

4- መዳን ወይም መጽደቅ በእምነት ነው፡፡

 የእግዚአብሔር ቃል በሮሜ 10 ቁ.9 ሲናገር / እምከመ፡ ተአምን፡ በአፉከ፡ከመ፡ክርስቶስ፡ውእቱ፡እግዚእ፡ወተአምን፡ በልብከ፡ከመ፡አንሥኦ፡ እግዚአብሄር እምውታን፡ተሐዩ፡፡ወልብን፡ ዘየአምን፡ቦቱ፡ይጸድቅ፡ወአፍኒ፡ዘየአምን፡ቦቱ፡የሐዩ፡፡ ” ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና፡፡ መጽሐፍ በእርሱ የሚያምን አያፍርም ይላልና፤” ሮሜ.10፤9-11፡፡ በቃሉ እንደተጠቀሰው የክርስቶስን ጌትነት በአፍ መመስከርና፣ ተሰቅሎ ለኃጢያት ስረየት የሚሆነውን ደሙን አፍስሶ፣ ሞቶ፣ ተቀብሮ፣ በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ ማመን ደግሞ ሁለተኛው ዋና ነገር ነው፡፡

5- ንስሐ መግባት!

 ኢየሱስም ራሱ ” ተነስሑ እስመ ቀርበት መንግስተ ሰማያት”- /መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ፡፡/ ወንጌል ዘማቴዎስ 4፤17፡፡ በሌላም በኩል ማመንና ንስሐ መግባት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡ በ ሌላ አነጋገር ንስሐ መግባትና ማመን የማይነጣጠሉ ናቸው ማለት ነው፡፡ ታዲያ ንስሐ ስንገባ ኃጢያታችን ይቅር እንደሚባል ተስፋ ተሰጥቶናል፡፡ ” በኃጢያታችን ብንናዘዝ  ኃጢያታችንን ይቅር ሊለን ከአመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡ኃጢያትን አላደረግንም ብንል ሀሰተኛ እናደርገዋለን፡፡ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም፡፡ ” / 1ዮሐ.1፤9-10/፡፡ መናዘዝ ማለት በስውርና በግልጽ፤ በስህተትና በድፍረት የሰሩትን ሐጢያት ለእግዚአብሔር ዘርዝሮ መናገር ማለት ነው፡፡

6- ጌታን መቀበል ምንድን ነው?

 ጌታን መቀበል የሚለው ቃል የመጣው ከዮሐንስ  ወንጌል ም.1 ቁ.11-13 ባለው  መሰረት ነው፡፡ ” ወለእለስ፡ ተወክፍዎ፡ወሀቦሙ፡ሥልጣን፡ውሉደ፡ እግዚአብሔር፡ ይኩኑ ለእለ፡አምኑ፡በስሙ፡፡ ” /የእርሱ ወደ ሆነው መጣ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም ፡፡ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው፡/ ይላል፡፡ ጌታችን  መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንቀበለው  /የምናስተናግደው /  የልባችንን በር በመክፈት ሲሆን በህይወታችን ላይ እርሱን እንደ ሊቀ ካህን፣ እንደ ነቢይ  የዘላለም ጌታና  ንጉስ አድርጎ መሾም ነው፡፡ራዕይ 3፤20

7- ዳግም መወለድ ማለት ምንድን ነው?

   ከላይ የዘረዘርናቸውን መንፈሳዊ እውነቶች በህይወቱ  በመታዘዝ ያደረገ ሁሉ ዳግመኛ ተወለደ ማለት ይቻላል፡፡ በዮሐንስ  ወንጌል ም.3 ቁ.3 እንደሚናገረው  ” ኢየሱስ ወይቤሉ፡አማን፡አማን፡እብለከ፡ዘኢተወልደ፡ዳገመ፡አይክል፡ርዕዮታ ለመንግሥተ፡ እግዚአብሔር፡፡” /…እውነት እውነት እልሀለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም ! ማለት ነው ትርጉሙ::

ለምሳሌ በዚህ ታሪክ ላይ የምናገኘው ኒቆዲሞስ  ሽማግሌ ነበር፣ የአይሁድ አስተማሪ ነበር፣ ይህ ብቻ አይደለም አጥባቂ ፈሪሳዊ  ነበር፣ ደግሞ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡ ረጅም ዘመን ብሉይ ኪዳንን ያስተማረ እንኩዋ ቢሆን፣ ወይም አለቃና በእድሜው የበሰለ የሚባል ሰው ቢሆን?  ዳግመኛ  ካልተወለድክ፤ የእግዚአብሔርን መንግስት አታይም ነው የተባለው፡፡ ስለዚህ ዳግም ሳንወለድ የምናደርጋቸው የትኞቹም ኀይማኖታዊ  እንቅስቃሴዎች  ለመዳናችን  ፋይዳ  የላቸውም:: አንተ ወንድሜ፣ አንቺስ እህቴ  ዳግመኛ ተወልዳችሁአል?

8- ንስሐ  ለገቡ ፣ ዳግመኛ ለተወለዱ  የተዘጋጁ  በረከቶች:-

  •  የዘላለም ህይወት ያገኛሉ፡፡ ዮሐ.3፤18፣ 1ዮሐ.1፡13
  •  ስማቸው   በህይወት  መዝገብ  ላይ ይጻፋል፡፡ ሉቃ.10፤20 ና ራዕይ 20፤15
  •   ከድቅድቅ  ጨለማ ወደሚደነቅ  ብርሀን  ይወጣሉ፡፡1ጴጥ.2፤9
  •   የክርስቶስ  ክብር  ተካፋይ  ይሆናሉ፡፡2ተሰ.2፤1
  •   አዲስ ፍጥረት ይሆናሉ፡፡ 2ቆሮ.5፤17
  •   ይጸድቃሉ፤  ይድናሉ ፡፡ ሮሜ.10፤ 9፣ ዮሐ.3፤16-18
  •   የእግዚአብሄርም ቤተሰብ ይሆናሉ፡፡ ኤፌ.2፤19፣ 1ዮሐ.5፤1

አስቸኳይ መልዕክት

“ኢየሱስ ይሰብክ ወይበል፡ተነስሑ እስመ ቀርበት መንግስተ ሰማያት!” ወንጌል ዘማቴዎስ 4፤17   /ኢየሱስም መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመረ /

    ለምወዳችሁ  ቤተሰቦቼና ወዳጆቼ

   በቅድሚያ የፍቅርና የከበረ ሰላምታዬን  በእግዚአብሔር ስም አቀርብላችሁዋለሁ፡፡ የጌታ ሰላምም ይብዛላችሁ፡፡

ዛሬ ይህንን አጭር መልዕክት ልጽፍላችሁ ያነሳሳኝ ምክንያት ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደሰማችሁት በክርስቶስ የማያምኑ ሁሉ የዘላለም ፍርድ ይጠብቃቸዋል ፤ያመኑት ግን የዘላለም ህይወትን አግኝተው መንግስቱን ይወርሳሉ፡፡ስለሆነም ይህንን እውነት ለምወዳቸው ሁሉ አስረግጦ መናገር በዚህ  የመጨረሻ መጨረሻ ጊዜ አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሁሉ ሐጢያት ሞተ፣ተቀበረ፣በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ፤ሞትንም ድል አድርጎ በተነሳ  በ40ኛው ቀን ወደ ሰማይ አረገ፣በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፡፡አሁን በቅርብ ተመልሶ ለፍርድ ይመጣል ፡፡ያን ጊዜም የዓለም መጨረሻው ይሆናል፡፡ ማንም ሰው ይህንን እውነት ቢያምንና ቢቀበል ከዘላለም ፍርድ ያመልጣል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን  ”ወይቤሉ ኢየሱስ አነ ውእቱ ፍናትኂ ወጽድቅ ወህይወት ወአልቦ ዘይመጽእ ኀበ አብ ዘእበለ እንተ ኃቤየ ”  / ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት ህይወትም ነኝ፡፡በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም::/ ብሉዋል፡፡ የዮሐንስ ወንጌል 14፤6፡፡ ይህም የሰው ልጆች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊመጡ የሚችሉበት እውነተኛና ብቸኛ መንገድ ክርስቶስ እንደሆነ በግልጥ ተቀምጡዋል፡፡

እንዲሁም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ቁጥር 16-18  ” በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ  ዓለሙን እንዲሁ ወዱዋልና፤ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አላከውምና፤በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሐር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል፡፡” ተብሎ ተጽፉዋል፡፡

ዋና ዋና ነጥቦቹ ፡-  1ኛ- ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ሰጥቷል፡፡

                       2ኛ- ክርስቶስ የመጣው ዓለምን ሁሉ ለማዳን ነው፡፡

                       3ኛ- በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ አይፈረድባቸውም፡፡

                       4ኛ- በክርስቶስ አምነው ያልዳኑ ሁሉ ፍርድ ይጠብቃቸዋል፡፡

  ስለሆነም ከልጅነት እስከ ዕውቀት በማናቸውም ሁኔታ የሰራነውን ሐጢያትና በደል ለእርሱ እየተናዘዝን ለሐጢያታችን የከፈለልንን ዋጋ ማመን አለብን፡፡ 1ዮሐ.1፤9 ሲናገር  “ኀጢያታችንን ብንናዘዝ ኀጢያታችንን ይቅር ሊለን ከአመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡”

እንግዲህ አንድ ሰው በተሰጠው የዕድሜ ዘመን ሁሉ አንድ ቀንም ይህንን ሳይቀበል፣ኀጢያቱንም ለክርስቶስ ዘርዝሮ ሳይናገርና ምህረትን ሳይቀበል፣ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ፤ ወይም ክርስቶስ በዳግም ምጽአቱ  ድንገት ቢመጣ ፤የዘላለም ሞት ነው የሚፈረድበት፡፡ የዮሐንስ ራዕይ 20፤15

እናንተም ወዳጆቼ ከዚህ የዘላለም ጥፋትና ስቃይ እንድትድኑ ይህንን የመዳን ወንጌል ቸል ልትሉት አይገባም፡፡

እስኪ ከዚህ በታች ያለውን የንስሐ ጸሎት ከልባችሁ ሆናችሁ ጸልዩ፡- ” ጌታ ሆይ እኛ ኃጢያተኞች ነን፤ከልጅነት ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ ባለማወቅና በድፍረት የሰራነውን ኃጢያት ሁሉ

 ይቅር በለን፡፡ጌታ ኢየሱስ  ሆይ  ስለ እኛ ሐጢያት መከራን እንደተቀበልክ ፣ደምህን እንዳፈሰስክ ና

እንደሞትክልን እናምናለን፡፡ ስለ ሐጢያታችን በፈሰሰው ደምህ ከበደላችን ሁሉ አንጻን ፤ልጆችህም

 አድርገን፡፡ ከዛሬዋ ዕለት ጀምረን አንተን  የህይወታችን ጌታና አዳኝ አድርገን 

ተቀብለንሐል፡፡በልባችንም ላይ ንገስ! ስማችንንም በህይወት መዝገብ ላይ ፃፍልን በኢየሱስ 

ክርስቶስ  ስም አሜን፡፡”

      ይህንን ታላቅ የንስሐ ጸሎት ከጸለያችሁ በሁዋላ ባደረጋችሁት ውሳኔ ፅኑ! በእምነታችሁም እንዳትደክሙ መፅሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብቡ፤ ዘውትርም ጸልዩ፡፡ ህይወታችሁን የሰጣችሁት ጌታ በነገር ሁሉ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ይረዳችሁማል፡፡አሜን፡፡

ማስታወሻ፡- እባክዎ እርሶ የተጠቀሙበትን መልዕክት ቢያንስ ለ10 ወዳጆችዎ ይላኩ!!!

 በወንጌል እንደተባለው  ” ወቀርበ ኢየሱስ ወተናገርሙ እንዘ ይብል ተውህበ ሊተ ኩሉ ኩነኔ ሰማይ ወምድር ሑሩ መህሩ ኩሉ አሕዛብ እንዘ ታጠምቅዎሙ በስመ አብ ፡ወወልድ ፡ወመንፈስ ቅዱስ ወመሀርወሙ ኩሉ ያዕቀቡ ዘአዘዝኩክሙ፡ወናሁ አነ ምስሌክሙ በኩሉ መዋዕል እስከ ኀልቀተ ዓለም ”  /ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው ስልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ ፡፡እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁአቸው ያዘዝሁዋችሁን እንዲጠብቁ  እያስተማራችሁአቸው ደቀ መዛሙርት አድርጉዋቸው ፤እነሆም እኔ እስከ ኣለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡/  ማቴዎስ 28፤18-20

  ንስሐ ገብተዋልን?

/ሌሎች እንዲጠቀሙበት share ያድርጉ /

ኢየሱስ ይሰብክ ወይበል፡ተነስሑ እስመ ቀርበት መንግስተ ሰማያት!” /ኢየሱስም መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመረ / ወንጌል ዘማቴዎስ 4፤17

     ምን ብለው ነው ንስሐ የሚገቡት?

/ እስኪ ከዚህ በታች ያለውን የንስሐ ጸሎት ባሉበት ቦታ ሆነው ለተወሰነ ደቂቃ ከልብዎ ሆነው ይጸልዩ / ፡-

” ጌታ ሆይ እኔ ኃጢያተኛ ነኝ፤ከልጅነት ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ ባለማወቅና በድፍረት የሰራሁትን ኃጢያት ሁሉ ይቅር በለኝ፡፡ጌታ ኢየሱስ ሆይ ስለ እኔ ሐጢያት መከራን እንደተቀበልክ ፣ደምህን እንዳፈሰስክ ና እንደሞትክልኝ እምናለሁ፡፡ ስለ ሐጢያቴም በፈሰሰው ደምህ ከበደሌ ሁሉ አንጻኝ ፤ልጅህም አድርገኝ፡፡ ከዛሬዋ ዕለት ጀምሬ አንተን የህይወቴ ጌታና አዳኝ አድርጌ አምኛለሁ ፣ ተቀብያለሁ፡፡በልቤም ላይ ንገስ! ስሜንም በህይወት መዝገብ ላይ ፃፍልኝ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን፡፡”

ይህንን ታላቅ የንስሐ ጸሎት ከጸለዩ በሁዋላ ባደረጉት ውሳኔ ፅኑ! በእምነትዎም እንዳይደክሙ መፅሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ያንብቡ፤ ዘውትርም ይጸልዩ፡፡ ህይወታችንን የሰጠነው ጌታ በነገር ሁሉ ከእኛጋር ይሆናል፤ይረዳንማል፡፡አሜን፡፡

ተጨማሪ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለማንበብ http://tehadesothought.blogspot.com ብለው ይጠቀሙ!

 ከሲኦል የተላከ ደብዳቤ

./ በ ሉቃስ ወንጌል 16፡19-31 ላይ ያለውን ታሪክ አንድ ሰው በዚህ መልክ አቅርቦታል፡፡  /

      ይድረስ በምድር ላይ  በአባቴ መኖሪያ ቤት ውስጥ እየኖራችሁ ላላችሁ አምስት የስጋ ወንድሞቼ፡፡ ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ ? ዛሬ ይህን ደብዳቤ ወደ እናንተ ልጽፍ ያነሳሳኝ ምክንያት አንድ ብርቱ ጉዳይ ላስታውቃችሁ ወስኜ ነው፡፡ እንደምታውቁት እኔ ወንድማችሁ በምድር ላይ በነበርኩ ጊዜ አንዳች ያልጎደለኝ  ሰው ነበርኩ፡፡ያማረኝን በልቼ .፣ያማረኝን ገዝቼ እኖር ነበር፡፡ አልፎ አልፎ ስለ ሞት ካሰብኩ ፡ ከሞትኩ በኋላ ቅዱሳን ሰማዕታት ከሲኦል ይታደጉኛል የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ ነገር ግን እዚያ ስሔድ ያጋጠሙኝ እውነታዎች ፈጽሞ እንዳሰብኩት አልነበሩም፡፡ ሁለሉ ነገረር ተደበላለቀብኝ ልወጣው የማልችለው ሲዖል ውስጥ ራሴን አገኘሁት፡፡ ክፋቱ ደግሞ ፈጽሞ በምንም መንገድ ልወጣ የማልችል መሆኔን ስረዳ ይህንን ደብዳቤ ልጽፍላችሁ ወሰንኩ፡፡

·         በመጀመሪያ ሲኦልና ገነት ከመሞት በሁአላ አለ ሲባል ሰምታችሁ ከሆነ እውነት ነው፡፡

·         በምድር ላይ እውነተኛ ንስሐ  ያልገቡ ና ትክክለኛ የህይወት ውሳኔን ያላደረጉ ሁሉ መጨረሻቸው ሲኦል ነው፡፡

·         አንድ ጊዜ ሲኦል ከተገባ በኋላ ጻድቃን ሰማዕታት ሊደርሱልን እንደማይችሉ ተረድቼአለሁ፡፡


ይህንንም እውነት ያወቅሁት ጻድቁ አባታችን አብርሐም ራሱን አነጋግሬው ነው፤ አላዛርን ሰድዶልኝ የምሰቃይበትን ነበልባል በጣቱ ጫፍ  ውሐ ነክሮ መላሴን  ጥቂት እንዲያበርድልኝ ተማጽኜው ነበር ፡ የእርሱ መልስ ግን በዚህ ያሉ ማናቸውም ወደዚያ ፡ ወዲያ በሲኦል ውስጥ ያሉ ወደዚህ እረፍት ቦታ እንዳይመጡ በመካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል ብሎ መልሶልኛል፡፡ የሉቃስ ወንጌል 16 ቁ.19-31 ፡፡ ስለዚህም ዝክር እየዘከራችሁ ከሆነ ፣ ወይም በስሜ የምታደርጉት ነገር ካለ ለመዳኔ አንዳች አይፈይድምና አትልፉ!!!

·         ከዚያም እናንተ ወደዚህ ስቃይ ስፍራ እንዳትመጡ እውነቱን ይነግራችሁ ዘንድ አላዛርን ወደ ምድር ወደ እናንተ እንዲልከው ተማጽኜው ነበር፡፡ ይህንም ያደረኩት ፈጽሞ ልታስቡት የማትችሉት ፡ነገር ግን እውነት የሆነ በዚህ ስላለ ፤ ሰው ከሞት ተነስቶ ካልነገራችሁ በቀር ላታምኑ ትችላላችሁ በሚል ነው፡፡ ጻድቁ አባታችን አብርሐም ግን እዚያ ያሉትን ነቢያት ና ሙሴ / የወንጌል መስካሪዎችን / ይመኑ እንጂ ሰው ከሞት ተነስቶ ቢመሰክርላቸውም አያምኑም አለኝ፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ወንጌል የሚነግሯችሁን ሰዎች አትናቁ! አውነት እነርሱ ጋር አለ፡፡ ከመሞታችሁ በፊት ምርጫችሁን አስተካክሉ፡፡ ምናልባት ሲኦል የሚያስገባችሁ መንገድ ላይ ከሆናችሁ ራሳችሁን  መርምሩ፡፡ እውነት የት እንደሆነ ፈልጉ፡፡ የሰው ይሉኝታ አይሰራችሁ፡፡ እዚህ ከመጣችሁ ስለእናንተ ማንም የሚሟገት የለም፡፡ በህይወት ሳላችሁ የመረጣችሁት ውሳኔ ነው የሚሰራው፡፡

·         በመጨረሻም የምጠይቃችሁ ነገር በተቻላችሁ መጠን ሁሉ ለዘመድ አዝማድ ፤ለጓደኞቻችሁ እና በዙሪያችሁ ላለ ህዝብ ሁሉ ይህንን እውነት አሳውቁ! ሁላችሁን እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ የሰራውን የዘላለም መዳን አምናችሁ ለመንግስቱ ያብቃችሁ፡፡


 ” የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ……አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ ፡፡ሰባኪው ከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል፡፡”  መክብብ 12፡1 ና 6-8

   በእንግሊዝኛ የድነት መልዕክቶች

     Start from Here!

  On June 6,1994,three American officers huddled in a bombshell crater on Utah Beach in Normandy ,France.Realizing the tide had carried them to the wrong place on the beach,the trio made an impromptu decision: ” We’ll start the battle from right here.” They needed to move forward from a difficult starting point. Saul found himself in a difficult place ,needing to make a dicision after meeting Jesus on the road to Damascus / Acts 9:1-20/.Suddenly,the location and direction of his life was revealed to him as a mistake,his prior life perhaps even feeling like a waste.

 Moving forward would be difficult and would require hard and uncomfortable work,perhaps even facing the Christian families whose lives he had torn apart.But he responded , ” LORD, WHAT DO YOU WANT ME TO DO ?”/v.6/ We often find our selves in unexpected places, places we never planned nor wanted to be. We may be drowing in debt , inhibited by physical barriers , or suffering under the weight of sin’s. Consequences. Whether Christ finds us this day in a prison cell or a place , whether He finds us broken and broke or absorbed by our own selfish desires, Scripture tells us to heed Paul’s advice to forgot what lies behind and to press forward toward Christ / Phil.3:13-14/.

  The past is no barrier to moving forward with Him. Are you paralyzed by your past? Have you drfted away from Christ? Or perhaps never even met Him ? Today is the day to begin anew with Christ,even if you’ve tried and failed before.

        From Randy kilgore’ s note ,For more teachings use this link, http:// tehadesothought.blogspot.com

    Don’t Delay

  For many years i spoke to my distant cousin about our need of a savior.When he visited me recently and I once again urged him to receive Christ,his immediate response was ” I would like to accept Jesus and join the Church , but not yet.I live among people of other faiths.Unless I relocate ,I will not be able to practice my faith well.” He cited persecution, ridicule ,and pressure from his peers as excuses to postpone his decision. His fears were legitimate, but i assured him that what ever happened, God would not abandon him.

 I encouraged my cousin not to DELAY but to trust God for care and protection.He gave up his defenses ,acknowledged his need of Christ ‘s forgiveness ,and trusted Him as his personal savior. When Jesus invited people to follow Him,they too offered excuses-all about being busy with the cares of this world / Luke 9:59-62/The Lord’s answer to them v 60-62 urges us not to let excuse deprive us of the most important thing in life the salvation of our souls. Do you hear God calling you to commit your life to Him? Do not delay. ” Now is the accept time ; behold,now is the day of salvation” 2 Cor.6:2.” For God so loved the world that He gave His only begotten Son, that whoever believes in Him should not perish but have everlasting life.” John 3:16 From Lawrence Darmani’s note

  Urgent Message 

 Dear family, friends and brothers and sisters :

  May the peace of the Lord be with you. I am writing to you that the end days are very near and we need to aware our destination before the days are ended. As you may already hard, Jesus Christ is the key for our salvation. Anyone who believes in Jesus Christ will get eternal life. If you don’t, there will be a punishment of Hell as a consequence. I believe this is very important to you to understand and respond accordingly before the end of your days.Jesus Christ was buried, and that He was raised on the third day. He appeared to hundreds of the brothers and sisters for forty days. He was lifted up into heaven and sat down at the right hand of God. This Jesus, who has been taken up, will come soon in just the same way as he ascend into heaven, and this will be the end of the world. Anyone who believes in this truth will escape God’s judgment and receive eternal life. The Bible says If we confess our sins, he is faithful and just and will forgive us our sins and purify us from all unrighteousness. Jesus said: “I am the way, the truth, and the life: no one comes unto the Father but by me.” (John 14:6). This clearly shows the only way to heaven is through Jesus. Similarly, John 3:16-18 said: “For God so loved the world that he gave his one and only Son, that whoever believes in him shall not perish but have eternal life. For God did not send his Son into the world to condemn the world, but to save the world through him. Whoever believes in him is not condemned, but whoever does not believe stands condemned already because they have not believed in the name of God’s one and only Son.” We have limited time on this world and death was completely unexpected. How will you use the precious time you have will determine where you spend eternal life. If you accept Jesus Christ as your personal savior and confess your sins, he is faithful and just to forgive you and to cleanse you from all unrighteousness and write your name on the Book of life. Unless you recognize Jesus as your savior and your Lord, you have NO right to approach God’s throne of grace. “For by grace are ye saved through faith; and that not of yourselves: it is the gift of God: Not of works, lest any man should boast.” (Ephesians 2:8-9). If anyone’s name was not found written in the book of life, he was thrown into the lake of fire (Revelation 20:15). You must first come by way of the cross of Jesus Christ, for there is only one way to God the Father, and that is through God the Son. “For there is one God, and one mediator between God and men, the man Christ Jesus” (1st Timothy 2:5).

   The major points from the verses are:God gave his begotten Son for the world Jesus come to this world to save all human kind Anyone who believe in Jesus will be savedAnyone who ignores this salivation will condemn. Trust Jesus Christ today! Here’s what you must do: Admit you are a sinner. “For all have sinned, and come short of the glory of God;” (Romans 3:23) Therefore, just as sin entered the world through one man, and death through sin, and in this way death came to all people, because all sinned (Romans 5:12) “If we say that we have not sinned, we make him a liar, and his word is not in us.” (1 John 1:10) Be willing to turn from sin (repent). Jesus said: “I tell you, no! But unless you repent, you too will all perish.” (Luke 13:5) Believe that Jesus Christ died for you, was buried, and rose from the dead.

  “For God so loved the world, that he gave his only begotten Son, that whosoever believeth in him should not perish, but have everlasting life.” (John 3:16) “But God commendeth his love toward us, in that, while we were yet sinners. Christ died for us.” (Romans 5:8) If you declare with your mouth, “Jesus is Lord,” and believe in your heart that God raised him from the dead, you will be saved” (Romans 10:9) Through prayer, invite Jesus into your life to become your personal Savior. “For with the heart man believeth unto righteousness; and with the mouth confession is made unto salvation.” (Romans 10:10)

  Dear God, I am a sinner and need forgiveness. I believe that Jesus Christ shed His precious blood and died for my sin. I am willing to turn from sin. I now invite Christ to come into my heart and life as my personal Savior. In Jesus name I pray, Amen.Once you pray this, believe Jesus cleans your sin. Read your Bible daily. Pray continuously.

Note: Please share this good news for 10 people and show how you care for them.

  Thanks Giving

Whereas the duty of all nations to acknowledge the providence of Almighty God, to obey his will, to be grateful for His benefits ,and humbly implore His protection ,aid and favors…Now therefore ,I do recommend and assign the 26th of November next, to be devoted by the people of these states to the service of that Great and Glorious Being.Who is the beneficent Author of all the good that was ,that is ,or that will be that we may then all united in rendering unto Him our sincere and humble thanks for His kind care and protection of the people of this country , and for all the great and various favors which He has been pleased of confer upon us.Our founding fathers openly recognized God. They were aware of our need for God if we were to be a healthy nation .George Washington said: ‘’ It is impossible to rightly govern the world without God and the Bible.’’ They know that if the nation was going to work its people needed to voluntarily live by God’s rules.Times have changed .We may be the only culture in the world that openly acknowledges God in our constitution,on our money , and on Thanks giving, but refused to allow God to be named in any of our public institutions.

As a nation we are working hard to push God out of our lives.Ignoring God isn’t unusual.The history of the world is a story of people turning away from God.Amazing,God hasn’t turned away from us yet.But if we do not repent,He will. Government can not turn us back to God. Turn back to God requires a change of heart.When get out hearts fixed,our priorities lineup, and things work better.You can get this change of hearts by giving up your old life and turning to God. He sent His Son Jesus to close this huge gulf between us and God.So when we turn to God in the name of Jesus, we are acceptable as if we never sinned-the Bible calls it being clothed with Jesus’ clothes in front of God. In the name of Jesus you can belong to God and busy yourself in His world. In the name of Jesus you can once again belong to others. When you belong to others, your life won’t be sucked dry –you’ll be like a mountain spring fuller and fresher than you ever imagined.That’s because you keep turning God to fill you up,and He has all the resources in the universe at His command. It’s like being wealthier than you could ever imagine.

 So I hope you will turn your face towards God this Thanks giving.Do more than Thank Him for good thanks giving will become a year-round event in your life.‘’ Blessed is the nation whose God is the Lord: Behold the eye of the Lord is upon them that fear Him, upon them hope in His mercy’’ , Psalm 33: 12,18.‘’Righteousness exalts a nation, but sin is a disgrace to any people.’’Proverb 14:34.‘’ For God so loved the world that He gave His only begotten Son that whosoever believeth in Him should not perish, but have everlasting life.’’ John 3:16.‘’ He that believeth on the Son hath everlasting life: and he that believeth not the Son shall not see life: but the wrath of God abideth on him’’ John 3:36.‘’ Whosoever shall call upon the name of the Lord shall be saved .’’ Romans 10:13 Thanks Giving PrayerDear God :Thank you for the wonderful gifts you have poured out on our nation.In the name of Jesus,who died for my sins,forgive me and forgive our nation for enjoying your gifts while trying to live without you. I repent of how I have been living and gratefully give my heart to you today. Help others in our nation to turn to you .Amen!

       Source: from Tract League blog If you want to read more use the Tract League website and WWW.lemekeru.com Or http://tehadesothought.blogspot.com

   ጸሎተ ሐይማኖት

የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሐይማኖት ጸሎት! በኒቂያ ጉባኤ በ 325 ዓ.ም. የተደነገገ፡፡

ሁሉን በሚገዛ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በእንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፡፡

ዓለም ሳይፈጠር የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፡፡

እርሱም ከብርሐን የተገኘ ብርሐን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የሚሆን : የተፈጠረ ያይደል የተወለደ : በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሆነ ሁሉ በእርሱ የሆነ : በሰማይና በምድር ካለው ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የሌለ : ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛንም ስለማዳን ከሰማይ ወረደ : በመንፈስ ቅዱስም ከቅድስት ድንግል ማርያም ስጋን ለበሰ: ሰውም ሆነ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ: መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረም በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ በክብርም ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም፡፡

     ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት በሚሰገድለትና በሚመሰገን ጌታ ሕይወት ሰጭ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በነቢያትም በተነገረ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን፡፡ በሁሉም ዘንድ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቡአት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡ ለኃጢአትም ስርየት : በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡ የሙታን ትንሳኤንና የሚመጣውን ዓለም ሕይወት በተስፋ እንጠባበቃለን፡፡ አሜን፡፡

     እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶድካሳዊት ቤተክርስቲያንም የተቀበለችው እውነት ይህ በመሆኑ ምዕመናን ሁሉ እንዲረዱት ፣እንዲያጠኑት ማገዝ ይጠበቅብናል፡፡ ስለ እኛ የተሰቀለውንና የሞተውን ደግሞ ከሙታን ተለይቶ የተነሳውን ጌታ ባለማመንና ባለማወቅ ሲኦል እንዳይገቡ ሁላችን የምንችለውን ሁሉ ስለ ወንጌል እናድርግ !!!


Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *